ዜና

2014 ሀገራችን የተፈተነችበት አመት ቢሆንም አንጸባራቂ ስኬቶችንም አስመዝግባበታለች – የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

Views: 48
ነሐሴ 2014 ዓ.ም በፈተና የታጀቡ ቢሆንም አንጸባራቂ ስኬቶች መመዝገባቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በሰጠው መግለጫ የሽብር ቡድኖቹ ህወሓትና ሸኔ በርካታ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥፋት ማድረሳቸውም ተነስቷል፡፡
በኢኮኖሚ ረገድም በርካታ የኢኮኖሚ አሻጥሮች መታየታቸውንም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ብታልፍም ስኬት ማስመዝገብ መቻሏን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ ገልፀዋል።
የሽብር ቡድኑ ህወሓት ሀገር ለማፍረስ ያደረገው ጥረት የተቀለበሰበት ሲሆን ኢትዮጵያዊያን መተባበር ያሳዩበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ አምስቱ የጳጉሜ ቀናትን ጳጉሜን በመደመር በሚል መርህ ሀሳብ ይከበራል ነው ያሉት ።
በዚህም ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃድ ቀን በሚል መርህ ይከበራል የተባለ ሲሆን በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ይሰራል ብለዋል።
ጳጉሜ 2 የአምራችነት ቀን በሚል የሚከበር ሲሆን የተለያዩ ግብርና ስራዎች እንደሚከናወን ገልጸዋል።
የሰላም ቀን ተብሎ በሚከበረው ጳጉሜ 3 የሰላም እሴቶች ይተዋወቁበታል ተብሏል።
ጳጉሜ 4 የአገልጋይነት ቀን በሚል የሚከበር ሲሆን በአዲስ አመት ሁሉም ተቋማት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለመ ነው ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።
በልዩ ሁኔታ የሚከበረው ጳጉሜ 5 የአንድነት ቀን ሲሆን ኢትዮጵያ አንድነቷን ጠብቃ የቆየች መሆኑን ለማሳየት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
ቀኑ ጠላታችንን አንድ ሆነን ማሸነፍ እንደምንችል ያሳየንበት እንደሆነ ለማሳየት ነው ተብሏል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *