ዜና

የተባበሩት መንግስታት ከኢትዮጵያ ጀርባ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር በቀጥታ በመደራደር የራሱን ሕጎች እየጣሰ መሆኑን ሾልኮ የወጣው መረጃ አመላከተ

Views: 47
የተባበሩት መንግሥት ከኢትዮጵያ ጀርባ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር በቀጥታ በመደራደር የራሱን ሕጎች እየጣሰ መሆኑን መረጃዎች አመላከቱ።
ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሳምንት ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሊቀመንበር ከሆነው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር አጠር ላለ ጊዜ ውይይት ማድረጋቸውን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስታፌን ዱጃሪች የጻፉት እና ሾልኮ የወጣው ኢ-ሜይል አረጋግጧል።
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከደብረፅዮን ጋር በድብቅ ውይይት ማድረጋቸው የተረጋገጠው ቃል አቀባዩ ከአምስት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ዜናዎችን ለሚሸፍኑ ጋዜጠኞች በጻፉት ደብዳቤ ላይ ነው።
አንድ የድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊ ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ቀጥተኛ ድርድር ማድረጉ ያልተጠበቀ እርምጃ ነው።
ህወሓት እስከ ዛሬ ድረስ በአሜሪካ መንግሥት የአሸባሪነት መዝገብ ላይ የሚገኝ እና የኢትዮጵያ መንግሥትም በአሸባሪነት የፈረጀው ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።
የአንቶኒዮ ጉቴሬዝን ድርጊት ያወገዙ አካላት፣ የተባበሩት መንግሥታት እንደ አይኤስ፣ አልሸባብ ወይም ቦኮ ሐራም ጋር በቀጥታ ይደራደራል ወይ ሲሉ መጠየቃቸውን ኢብኮ አስነብቧል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *