ዜና

ዋሺንግተን ታይዋንን ማስታጠቅ እንድታቆም ቻይና ጠየቀች

Views: 41
ዋሺንግተን ታይዋንን ማስታስጠቋን የምትቀጥል ከሆነ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ቻይና አስጠነቀቀች፡፡
የባይደንን አስተዳደር ዋሺንግተን 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የሚገመት የመሣሪያ ሽያጭ ለታይዋን ለማቅረብ የሀገሪቷን ሕግ አውጪ አካል ለመጠየቅ ማቀዱን ፖሊቲኮ አስነብቧል።
ይህን ተከትሎም በአሜሪካ የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሊዩ ፔንግዩ ዋሺንግተንን አስጠንቅቀዋል።
ቃል አቀባዩ የአሜሪካ ዕቅድ “የአንድ ቻይና”ን ፖሊሲ እንዲሁም በአሜሪካ እና በቻይና መካከል የተደረሱ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነቶችን የሚጥስ ነው ብለዋል፡፡
መሰል ስምምነቶች “ተገንጣዮችን ያበረታታሉ” ፤ “በቀጣናው ያለውንም ውጥረት ያባብሳል”ም ነው ያሉት፡፡
በመሆኑም አሜሪካ ከታይዋን ጋር ያላትን ወታደራዊ ግንኙነት እና የመሣሪያ ሽያጭ በአስቸኳይ ታቁም ሲሉ መጠየቃቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡
ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ቻይና ሉዓላዊነቷን እና ደኅንነቷን ለመከላከል አስፈላጊ እና ጠንካራ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቀዋል።
እንደ ፖሊቲኮ ዘገባ የባይደን አስተዳደር ለታይዋን የ355 ሚሊየን ዶላር ፀረ-መርከብ ሚሳኤሎች እንዲሁም የ85 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር የዓየር መቃወሚያ ሚሳኤሎችን ለመሸጥ አስቧል፡፡
በተጨማሪም በ655 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የክትትል ራዳር ለማቅረብ ማቀዱም ነው የተሰማው፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *