ዜና

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

Views: 39

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሰጠ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ የክብር ዶክትሬቱን የሰጣቸው÷ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር እየኖሩ ያሉ እንዲሁም ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ ታላቅ ዓርዓያ ሰብ በመሆናቸው ነው ብሏል፡፡
እንዲሁም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ÷ በአትሌቲክስ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ፋና ወጊ አትሌት እና ለህብረሰተብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት እየተጋች ያለች የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት በመሆኗ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *