ዜና

ብሪታኒያ ህወሓት በመቀሌ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ላይ የፈፀመው ዝርፊያ ተቀባይነት የለውም አለች

Views: 40

ህወሓት በመቀሌ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ላይ የፈፀመው ዝርፊያ ተቀባይነት የለውም ስትል ብሪታኒያ ገለፀች።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም የህወሓት ታጣቂዎች መቀሌ ወደሚገኘው መጋዘኑ በሀይል በመግባት 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ የያዙ 12 ቦቴ መኪናዎችን መዝረፋቸውን ማስታወቁ ይታወሳል።
የብሪታኒያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጉዳዩን አስመልክቶ በትዊተር ገፃቸው በኩል ባወጡት መግለጫ፥ የህወሓት ዝርፊያ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል።
የዝርፊያ ድርጊቱም በክልሉ የሚከናወነውን የረድኤት ስራ እንደሚጎዳው ነው ያመለከቱት።
የሰብዓዊ አቅርቦት ስራ ሊያስተጓጉል እንደማይገባ አመልክተዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *