ዜና

“ኽ” ዬን መልስልኝ ግልጽ ደብዳቤ፣ ለአትሊት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፤

Views: 99

                                                                                                                                                                                                                                                                                             ከመስፍን ታደሰ (ዶክተር፣ ኮለምበስ፣ ኦሃዮ)

 ሻለቃ፣ አንተዋወቅም። እኔ በስራህና በሞያህ አውቅሃለሁ። በሩጫ ውድድርም ተደናቂ አትሌት ስለሆንክ አድናቂህም ነኝ፣ በተለይም ሌላው ተወዳጅ አርቲስት፣ የሙዚቃ ባለሙያ፣ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) የአንተን፣ የቀነኒሳን እና የስለሺን ከሌሎች አትሌቶች ጋር ያደረጋችሁትን የሩጫ ውድድር ከሙዚቃ ጋር አዋህዶ ባቀረበበት ቀን ቢሮዬ ቀኑን ሙሉ አዳምጠው ነበር። ከጥቂት ቀናት በኋላ የኬንያው ጋዜጣ “ዴይሊ ኔሽን [The Nation, Sunday August 22, 2004]” በመጀመሪያው ገጹ ላይ የሶስታችሁን ድል ከፎቶግራፍ ጋር በሚከተለው ርዕስ ስር “salvage dented Kenyan pride; Ethiopian runners bury Kenyans” አውጥቶት ስለነበር ያን የጋዜጣ ክፍል ቆርጬና ቢሮዬ በመስታወት ውስጥ ከጀርባዬ ሰቅየዋለሁ፣ የዘላለም ማስታወሻ አድርጌዋለሁ።

ይህን ደብዳቤ የምድፍልህ ከአምስት ወይም ስድስት ዓመት በፊት በየጊዜው ከኢትዮጵያ የሚሰራጩትን ልዩ ልዩ ፊልሞች፣ ተውኔቶች፣ ንግግሮች፣ ወዘተርፈ፣ ሳይና ሳዳምጥ በተደጋጋሚ ለጆሮ ተስማሚ ያልሆኑ፣ የሚሰቀጥጡ፣ ቃሎችን ሳዳምጥ ቆይቼ አንድ ቀን ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ብዬ አንድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ወዳጄን መልስ አገኝ ይሆናል በሚል ግምት ልጠይቀው ወሰንኩ። ጥያቄዬን በኢሜይል ላኩለት፣ ጥያቄው ይህ ነበር፣

ለመሆኑ          

እንዴት              ተተኩ?

የሚል ነበር። ያ ወዳጄ ይህ ሊሆን የቻለው ታዳጊው ወጣት ታዋቂ የሆኑ የሰዎችን ቃሎችና አንዳንዴም ንግግሮች ትክክለኛ አባባል ነው ብሎ ስለሚወስደው ነው አለኝ።

ትምህርት ቤት ያሉ አስተማሪዎች ይህንን አያርሙትም ወይ? ብዬ አልጠቅሁትም ያን ወዳጄን። እኛ ልጆች ሳለን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ “በመዠመሪያ፣ ዠምሮ፣ ወዘተ” ሲሉ እኛ “በመጀመሪያ፣ ጀምሮ፣ ወዘተ፣” እያልን  እያስተካከልን ነው ያደግነው።

ሻለቃ ኃይሌ አንተ አንዱ ታዋቂና የኢትዮጵያ ባለውለታ ነህ። እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዛሬው ቀን (June 25 2021 GC; ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓም) ከታሪኩ ጋንካሲ ጋር ያደረግኸውን ቃለ ምልልስ ሳዳምጥ የሚከተሉትን የቃላቶች አወጣጥ ስሰማ አንተ አስተዋጽዖ ካደረጉት አንዱ ስለመሰልከኝ ከቻልክ ለወደፊት እያስተካከልክ ወጣቱን ብታስተምር ብዬ በማሰብ ልጠይቕህ ነው ይህንን ግልጽ ደብዳቤ በዚህ የድህረ ገጽ አውታር እንዲሰራጭና እንድታየው ያደረኩት። ታየዋለህ፣ ታነበዋለህ ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ። የተጠቀምካቸውን ቃላቶችና መባል የነበረባቸውን አስፍሬአለሁ፣ ሌሎች ወጣቶች ያበሏሿቸውንም እንዲሁ።

 

 

የአንተ አባባል መባል እና መጻፍ ያለበት
እምልክ እምልህ ወይም እምልኽ
መጥተክ መጥተህ ወይም መጥተኽ
ስጠራክ ስጠራህ ወይም ስጠራኽ

 

ሌሎች ወጣቶች ያበሏሿቸው መባል እና መጻፍ ያለበት
መጣክ መጣህ ወይም መጣኽ
ልንገርክ ልንገርህ ወይም ልንገርኽ

 

ይህንን ምልጃ በ June 25 2021 GC (ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓም) ብጽፈውም እስከ ዛሬ ቀን ድረስ ለሚዲያ አላኩትም ነበር። መልስ አልጠብቅም፣ ወደፊት ከምታደርገው ቃለ ምልልስ መልስኽን አገኛለሁ ብዬ በተስፋ እጠብቃለሁ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *