ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

Views: 105
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሁሉም ክፍለ ከተማዎች መሠጠት ተጀምሯል።
በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር እየወሰዱ ሲሆን÷ ፈተናው ለ3 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል።
የፈተና ደህንነት ለመጠበቅ እና የፈተናውን ሂደት ለመከታተልም ቀደም ሲል የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት 10 የፀጥታ አካላት ማሰማራቱ ተገልጿል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷በዚህም 71 ሺህ 832 የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *