ዜና

መንግስት ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ከወሰደው የግጭት ማቆም ውሳኔ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል የሚጓጓዘው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል – ተመድ

Views: 67

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ በተገቢው ሁኔታ እንዲደርስ ከወሰደው የግጭት ማቆም ውሳኔ በኋላ ወደ ክልሉ የሚጓጓዘው የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ፡፡
ከፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚጓጓዘው የምግብ ድጋፍ እየደረሰ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል፡፡
በዚህም የዓለም የምግብ ፕሮግራም በወር 5 ነጥብ 9 ሚሊየን ሰዎችን መመገብ የሚችል በቂ ምግብ ማቅረቡን ተመድ በትዊተር ገጹ አስታወቋል።
የፌደራል መንግስት ከወራት በፊት በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ወደ ክልሉ እንዲደርስ በማሰብ የግጭት መቆም ውሳኔ መወሰኑ ይታወሳል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *