ዜና

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የባይደንን አስገዳጅ የኮቪድ ክትባት ሃሳብ ውድቅ አደረገ

Views: 29

አሜሪካውያን በኮቪድ-19 ክትባት ላይ የተለያየ አቋምን ይዘዋል።

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በግዙፍ ኩባንያዎች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ኮቪድ መከላከያ እንዲከተቡ አልያም የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል እንዲያደርጉ እና በየሳምንቱ ይመርመሩ የሚለውን የፕሬዝደንት ጆ ባይደን ትዕዛዝን ውድቅ አደረገ።

የአሜሪካ ከፍተኛው የፍትሕ አካል ይህ የፕሬዝደንቱ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ ነው ብሏል።

ፕሬዝደንቱ ይህ መመሪያ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ያግዛል ይላሉ።

የባይደን አስተዳደር በርካታ ቁጥር ባላቸው ኩባንያዎች ውስጥ ክትባትን ግዴታ ማድረግ በቀጣይ ስድስት ወራት የ6 ሺህ 500 ሰዎችን ሕይወት እንደሚታደግ እና ከ250ሺህ በላይ ሰዎች ሆስፒታል እንዳይገቡ ያደርጋል ሲል ተንብዮ ነበር።

ተቀባይነታቸው እየቀነሰ የመጣው ባይደን፤ እርምጃው የሠራተኞችን ሕይወት ለመታደግ የተላለፈ ነበር በማለት በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ትዕዛዝ ቅር መሰኘታቸውን ተናግረዋል።

ምንም እንኳ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዛቸውን ውድቅ ቢያደርግባቸውም፤ ፕሬዝደንት ባይደን ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸውን፣ ደንበኞቻቸውን እና ማኅብረሰቡን ለመጠበቅ ሲባል ሠራተኞቻቸውን እንዲያስከትቡ ጥሪ አቅርበዋል።

የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በደስታ ተቀብለው፤ ክትባት መውሰድ ግዴታ መሆኑ፤ “ምጣኔ ሃብቱን የበለጠ ይጎዳል” ብለዋል።

“ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ድጋፍ ባለመስጠቱ ኩረት ተሰምቶናል” ብለዋል የቀድሞ ፕሬዝደንት ባወጡት መግለጫ።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገው የፕሬዝደንት ባይደን ትዕዛዝ ሠራተኞች የኮቪድ ክትባትን መውሰድ አልያም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን ግዴታ ያደርግ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ሠራተኞች በየሳምንቱ በራሳቸው ወጪ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርጉ ያስገድዳል።

ይህ የፕሬዝደንቱ ትዕዛዝ ተፈጻሚ ቢሆን ኖሮ ከ100 ባላነሱ ኩባንያዎች ውስጥ የሚሰሩ ከ84 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆን ነበር።

በርካታ ሪፓብሊካኖችን ጨምሮ የባይደን አስተዳደር ተቃዋሚዎች፤ ፕሬዝደንቱ በሕግ የተሰጣቸው ኃላፊነትን እየተላለፉ ነው ይላሉ።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “ኮቪድ-19 በመኖሪያ ቤት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በስፖርት ዝግጅቶች እና በየትኛው ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች ይሰራጫል” ካሉ በኋላ ሠራተኞችን ብቻ ላይቶ ይህን ትዕዛዝ ተፈጻሚ ማድረግ በተቀጣሪዎች ሕይወት እና ጤና ላይ ጥስት መፈጸም ነው ብሏል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የባይደንን ትዕዛዝ 6 ለ 3 በሆነ ድምጽ ነው ውድቅ ያደረገው።

እስካሁን ድረስ 60 በመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን ሙሉ ከትባት ወስደዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com