ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

Views: 37
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አኒከን ሁይትፌልድት ጋር በስልክ ተወያዩ።
አቶ ደመቀ ለኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ እየታዩ ስላሉ ለውጦች ገለጻ አድርገዋል።
ኖርዌይ በጥር ወር በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆና መመረጧን ተከትሎም የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፥ ኖርዌይ የምክር ቤቱ ፕሬዚደንትነቷን በመጠቀም የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግባር ሚዛናዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ እንደምትመለከተው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አቶ ደመቀ አክለውም፥ አገሪቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንትነቷ በጎ ሚና እንደምትጫወት ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልፀውላቸዋል።
የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አኒከን ሁይትፌልድት ፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ለሰጡት መግለጫ አመስግነው ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ጥረትን አድንቀዋል።
አኒከን ሁይትፌልድት ፥ በቀጣይም ኖርዌይ ኢትዮጵያን በተመድ አጀንዳ የማድረግ እቅድ እንደሌላትም ማስታወቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com