ዜና

ኢጋድ በሶማልያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘ

Views: 42
የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) በሶማልያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት በጽኑ አወገዘ።
በሶማልያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በአጥፍቶ ጠፊ ግለሰብ የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው ብዙኃንን ለሞትና ለከፍተኛ ጉዳት የዳረገውን የሽብር ጥቃት በጥብቅ እንደሚያወግዙት አስታውቀዋል።
ለተጎጂዎችና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን የተመኙት ዋና ጸሐፊው ኢጋድ ለሶማልያ መንግሥትና ህዝብ ማንኛውንም ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል።
ዛሬ ከከሰዓት በፊት በሞቃዲሾ ኤደን አየር ማረፊያ አቅራቢያ የጸጥታ አካላትን ኢላማ አድርጎ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ወታደሮችን ጨምሮ 10 ሰዎች ሲሞቱ ብዙዎች ደግሞ መጎዳታቸው ተዘግቧል። (ኢዜአ)
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com