ዜና

በአጣዬ በአሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሃት የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

Views: 26
የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በአጣዬ ከተማ በአሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሃት የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ።
የከተማዋ አስተዳድር ከንቲባ አሳልፍ ደርቤ እንደተናገሩት፥ በከተማዋ ህወሃትና ሸኔ በጋራ ሆነው 420 መኖሪያ ቤቶችና 50 ግሮሰሪና ሆቴሎችን አውድመዋል፤ ከ250 በላይ ሰዎችንም ገድለዋል።
ከተማዋን መልሶ ለመገንባትም እስካሁን በተሰራ ስራ የ45 ቤቶች ግንባታ በይፋት ልማት ማህበርና በመንግስት መጀመሩን ተናግረው፥ ቀሪ ቤቶችን ለመገንባት ሰራዎች ተጀምረዋል ብለዋል ከንቲባው።
በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በአማራ ልማት ማህበር አስተባባሪነት 160 ሺህ ዶላር በሆነ ወጪ በመጀመሪያ ዙር ዘጠኝ ቤቶችን ለመስራት ተረክበዋል ነው ያሉት ።
የፈረሱ ቤቶችን የመገንባት ስራው ይቀጥላል ያሉት የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ማርቆስ ተገኝ፥ ተጨማሪ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ ተይዟልም ብለዋል ።
የአማራ ልማት ማህበር የዋና ስራ አስፈጻሚ ልዩ ረዳትና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አበረ መኩሪያ በበኩላቸው ዳያስፖራው የደረሰውን ጉዳት ለሌሎች በማሳወቅ ከተሞችን መልሶ ለመገንባት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com