ዜና

ኢትዮጵያን የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለማድረግ ድርድሩ ቀጥሏል

Views: 37
ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ድርድር ላይ ትገኛለች ፡፡
የአለም የንግድ ስርዓትን እየመራ የሚገኘው የአለም ንግድ ድርጅት ዛሬ ላይ የአባል ሃገራቱ ቁጥር 164 የደረሰ ሲሆን፥ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የድርጅቱ አባል ያልነበሩ ዘጠኝ ሀገራት ደግሞ በድርድር አባል የመሆን ሂደት ላይ ናቸው፡፡
በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ግንኙነትና ድርድር ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ምንዳዬ፥ መስራቾቹ ሃብታም የሚባሉ ሀገራት እንደነበሩ ገልፀው፥ በፈረንጆቹ 1947 ድርጅቱ ሲመሰረት አብዛኞቹ አፍሪካ ሃገራት በቅኝ ግዛት ውስጥ እንደነበሩ ያስታውሳሉ።
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ግዛት ስር ስላልነበሩ በድርጅቱ ምስረታ ላይ አልተሳተፉም። በዚህ ምክንያት አብዛኛው ህጎች እና መስፈርቶች የተጻፉት በቅኝ ገዢዎች ወይም ከአፍሪካ ውጭ በሆኑ ሃገራት መሆኑን ነው የሚናገሩት።
ከዚ በኋላ በነበሩ የድርድር ሂደቶች የአፍሪካ ሃገራት እንዲሳተፉ ተደርጓል።
አብዛኛው የዓለም ንግድ እንቅስቃሴ የሚዘወረውና የሚወሰነው በዚሁ ድርጅት ነው፤ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የድርጅቱ አባል ያልሆኑ ሀገራትም ቢሆኑ ድርጅቱ በሚያወጣቸው መመሪያዎች የግድ ይመራሉ፤ አባል አለመሆን የሚፈጥረው ተግዳሮትም ቀላል አለመሆኑ ይነሳል፡፡
የኢትዮጵያ ምርቶችን የጤና ደህንነት እና ጥራት በሚሉ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ ሃገራት እንዳይገቡ ይደረጋል፤ የኢትዮጵያ ምርቶች በሌሎች አባል በሆኑ ሃገራት ዙረው ሲገቡ ግን ተቀባይነት አላቸው ፤እንዲሁም የድርጅቱ አባል መሆን የሚመጡ አለማቀፍ ባለሃብቶችን በብዛት ይስባል፣ መተማመንም የሚፈጥር ነዉ ።
ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን 18 ዓመታትን የፈጀ የድርድር ሂደት ያሳለፈች ሲሆን፥ ውሳኔ በጊዜ መስጠት አለመቻል፣ ቸልተኝነት የተስተዋለበትና የአባልነት ጊዜውን ያራዘመ የድርድር ሁኔታ ስለማለፉ ይነሳል፡፡
የድርድር ሂደቱ ላይ እየተሳተፉ ያሉት አቶ ሙሴ፥ ኢትዮጵያ አሁን ላይ የድርጅቱ አባል ለመሆን ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት 2019 ሰነዶችን በማዘጋጀት ወደ ሂደቱ ተመልሰናል ብለዋል፡፡
የድርድር ሂደቱም አሁን ላይ በተለያዩ መመዘኛ በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ሙሴ፥ የአለም ንግድ ድርጅት አባል መሆን የመጨረሻ ግብ እንዳለመሆኑ የሀገርን ጥቅም ማስጠበቅ ትልቅ ትኩረት ይሰጠዋልም ነው ያሉት፡፡
አሁን ላይ ወደ 44 ሃገሮች በኢትዮጵያ ለማልማት ፍላጎታቸው የገለፁ ሲሆን፥ ይህ እየጨመረ የሚሄደውን ስኬታማነትን ለማስቀጠል የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ማሳደግና ኢኮኖሚው ጠንክሮ እንዲወጣ ማድረግ ትልቁ የቤት ስራ ሆኖ ይቀጥላል ተብሏል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com