ዜና

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እልባት የሚሹ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መስራት አለብን አሉ

Views: 45
በሚያለያዩን ጉዳዮች ላይ ከማተኮር ይልቅ እልባት የሚሹ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መስራት አለብን ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ጥፋት በየትኛውም መመዘኛ በአጭር ጊዜ የሚካካስ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዋና ዓላማችን በማውጣት ሊከፋፍለንና ሊያዳክመን የሚችልን ጉዳይ ወደ ጎን በማቆየት አንድነታችንን አጠናክረን ዳግም ወረራ እንዳይመጣብን ማድረግ ያስፈልገናል ብለዋል።
አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ክልል በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች አስነዋሪ ድርጊቶችና ጥፋቶች እንደፈጸመ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የወደሙትን መልሶ የመገንባት ሂደት የሁሉም ድርሻ ሊሆን እንደሚገባው ጠቅሰው የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ማቋቋምና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማትን የመጠገን ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com