ዜና

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 6 እንደሚቀጥል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስታወቀ

Views: 114
የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙን ተከትሎ የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማን ከታህሳስ 26 ጀምሮ እየተቀበለ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እስከ መጪው ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጥቆማ መቀበሉን እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡
በሂደቱ ጠቋሚዎች የሚያነሷቸው እና እንዲብራሩላቸው የሚፈልጓቸው ጉዳዮችን አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥያቄዎችን እየጠየቁ ይገኛሉ ያለው ምክር ቤቱ፥ ዜጎች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መከታተላቸውንና ጥያቄ ማቅረባቸውን አድንቋል፡፡
የሚጠቆሙት ዕጪዎች ከሚኖራቸው ከፍተኛ ሃገራዊ ኃላፊነት አንፃር ጠቋሚዎች ስለሚጠቁሙት ሰው የተሟላና ተጨባጭ ዕውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ አመላክቶ፥ በዚህ ደረጃ ታስቦበትና ዝግጅት ተደርጎበት ጥቆማ ማካሄድ እንደሚገባ አሳስቧል።
አንድ ጠቋሚ መጠቆም የሚችለው አንድ ግለሰብ ብቻ መሆኑንም ም/ቤቱ አስገንዝቧል።
በተጨማሪም አንድ ዕጩ በስንት ሰዎች ተጠቆመ የሚለው አሃዝ ለዕጩ ኮሚሽነሮች መረጣ እንደ መሥፈርት ያልተቀመጠ በመሆኑ፥ አንድን ግለሰብ ደጋግሞ መጠቆም ተቀባይነት እንደሌለውም አሳውቋል፡፡
በዚሁ መሠረት በተዘጋጀው ቅጽ መሠረት ብቻ ጥቆማውን መስጠት የሚቻል መሆኑን ም/ቤቱ በድጋሜ አሳስቧል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com