ዜና

በብሔራዊ መግባባት ውይይቱ ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን ለመፍታት መዘጋጀት እንደሚገባ ኢዜማ ገለጸ

Views: 52
የብሔራዊ መግባባት ውይይቱ ዋና ዋና ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን የሚፈታ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ኃይሎች በጠረጴዛ ዙሪያ ችግሮችን ለመፍታት መዘጋጀት እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ገለጸ።
ሁሉም ኃይሎች በጠረጴዛ ዙሪያ በብሔራዊ መግባባት ውይይቱ ዋና ዋና ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን ለመፍታት መዘጋጀት ይገባቸዋል ሲሉ የኢዜማ ሊቀ መንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ለኢፕድ ገልጸዋል ፡፡
ውይይት እንደሚያስፈልግ መተማመን ላይ መደረሱ በጣም ትልቅ እርምጃ ነው፤ ብሔራዊ ውይይቱ በአገራችን ኢትዮጵያ ከተከናወኑ ወሳኝ ነገሮች ከምርጫው፣ ከግድቡ መሞላት እና ከመንግሥት ምስረታው ባልተናነሰ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት ብቻ ሳይሆን ሰላሳና አርባ አመታት ሲንከባለሉ የመጡ ምርጫ የማይፈታቸው ፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እንዳሉ የጠቀሱት አቶ የሺዋስ እነዚህ ጉዳዮች በህገ መንግሥት፣ በፌዴራል አወቃቀር፣ በሰንደቅ አላማና በመሳሰሉት የሚገለጹና ፖለቲካው ሲስተካከል አብረው ይስተካከላሉ ብሎ ፓርቲያቸው እንደሚያምን ተናግረዋል።
ሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ ሚዲያዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎችና መንግሥት በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ያስፈልጋል በሚለውና በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ላይ ፍጹም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይህ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዕድል መሆኑን አቶ የሺዋስ አመልክተዋል።
የሚነሱ አጀንዳዎች፣ በብሔራዊ መግባባት ውይይቱ ላይ እነማን መሳተፍ እንደሚገባቸው እንዲሁም አተገባበሩን በሚመለከት በዝርዝር የሚኬድባቸው ነገሮች ናቸው። የብዙ አገራት ልምዶችን በመመልከት እነዚህን ነገሮች ማስተካከል እንደሚቻል ገልጸዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com