ዜና

በሳምንቱ የ10 አገራት አምባሳደሮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሀገሪቱን ተደማጭነት የሚያሳድግ ነው -አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

Views: 60
አንዳንድ ምዕራባዊያንና የአውሮፓ ሀገሮች ዲፕሎማቶች ከኢትዮጵያ ሲሸሹ የ10 አገራት አምባሳደሮቹ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሀገሪቱን ተደማጭነት ይበልጥ እንደሚያሳድገው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቃባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ሳምታዊ መግለጫ 10 የተለያዩ ሀገራትን አምባሳደሮችን ሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ማቅረባቸውን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴም ለአምባሳደሮቹ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ በተመለከተ መብራሪያ መስጠታቸውን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡
የፈረንጆቹ ዓመት 2021 በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ፈተናዎች የነበሩበትና ሀገሪቱ በብልህነት በአንድነትና ለድል የበቃችበት ግዜ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በተለይም መላው ኢትዮጵያዊያን ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ለሀገሪቱ አብሮነታቸውን ያሳዩበት ወቅት ነበር ብለዋል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው፡፡
በታላቁ የህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ድርድርም ወደ አፍርካ ህብረት እንዲዛወር ለማድረግ የተደረገው ጥረት ከፈተናዎች መካከል ከጥቅቶች አንዱ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡
በሰሜን የሀገራችን ክፍል ከነበረው ግጭት ባሻገር የሱዳንና ግብጽ ጫና ከባድ ፈተና እንደነበሩ አምባሳደር ዲና ተናገረዋል፡፡
በቀጣይ በፈረንጆቹ 2022 እቅዳችን ሉዓላዊነታችንና ነጻነታችንና በማስከበር ከወዳጅ ሀገሮች ጋር ያለንን ግኑኝነት በማጠናከር ፤ በህዝቡ መካከል ውይይቶችንና ስምምነቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንሰራለን ብለዋል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com