ዜና

አሸባሪው ህወሓት መስጂዶችን የጦር ማዘዣና ምሽግ አድርጎ ተጠቅሟል

Views: 54
አሸባሪው የህወሓት ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው የአፋርና አማራ ክልሎች የሚገኙ መስጂዶችን የጦር ማዘዣና ምሽግ አድርጎ መጠቀሙን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ አስታወቀ።
የአብይ ኮሚቴው አባልና የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መሐመድ ካሳ እንደገለጹት፤ አሸባሪ ቡድኑ በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች መስጂዶችን የጦር ማዘዣና ምሽግ አድርጎ ተጠቅሟል ብለዋል።
በመስጂዶች ላይ እጅግ አስነዋሪ ድርጊት መፈጸሙንም ጠቁመዋል። የሰው ልጅ ለፈጣሪው ጸሎትና ምስጋና የሚያቀርብበትን የእምነት ተቋማትን የጦር ምሽግ ማድረግ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ህገወጥ ድርጊት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
በቀጣይም የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር በማጥናት ህጉ በሚፈቅደው መሰረት እስከ ዓለም አቀፍ ተቋማት ድረስ የጉዳቱን መጠን የማሳወቅ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀው፤ ተገቢውን ጥናት በማድረግ የተጎዱ ቤተ እምነቶችንና ሃብቶችን መልሶ የመገንባት ስራ እንደሚከናወን ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የኢትዮጵያ ቤተ-እምነቶች ሲወድሙ ዝምታን መምረጣቸው ተገቢ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com