ዜና

ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ልትሾም ነው

Views: 154
ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እንደምትሾም የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ አስታወቁ።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከኬንያ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ቻይና የምትሾመው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ በቀጣናው ያሉ አገራት የሚያጋጥሟቸውን የፀጥታ እና ደኅንነት ስጋቶችን ለመቀልበስ የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በቀጣናው ሰላማዊ ድርድሮች እንዲካሄዱ ቻይና ሁኔታዎችን የሚያመቻች ተጠሪነቱ ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆነ ልዩ መልዕክተኛ በቅርቡ እንደምትልክ ማስታወቋን የአገሪቱ የዜና አውታር ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com