ዜና

ሩሲያና ኢንዶኔዢያ ኢትዮጵያዊያንን እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ አሉም

Views: 37

ምዕራባውያን የዲፕሎማሲ ጫና በበረታበት ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን የነበሩ አገራት የገና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላለፉ፡፡

መልካም ምኞታቸውን ካስተላለፉ አገራት መካከል ሩሲያና ኢንዶኔዢያ በአምባሳደሮቻቸው በኩል ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለታላቁ የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆነችው ሩሲያ በአምባሳደሯ በኩል በአማርኛ ቋንቋ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቷን ያስተላለፈች ሲሆን የምዕራባውያን የዲፕሎማሲ ጫና በበረታበት ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን ሆና አቋሟን ስታሳውቅ የነበረችው ኢንዶኖዢያም ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለታላቁ የገና በዓል አደረሳችሁ ስትል በአምባሳደሯ በኩል መልካም ምኞቷን ገልፃለች፡፡

መልካም ምኞታቸውን ለኢትዮጵያዊያን የገለጹት ሩሲያና ኢንዶኖዢያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋም በመልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com