ዜና

ወደ ኮምቦልቻ ከነገ ጀምሮ የመንገደኞች በረራ ይጀመራል

Views: 73
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ታኅሣሥ 27 ጀምሮ ወደ ኮምቦልቻ እለታዊ የበረራ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ በማኅበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው ከአዲስ አበባ የሚነሳው እለታዊ የበረራ አገልግሎቱ ረቡዕ ይጀምራል፡፡
የሽብር ቡድኑ ትሕነግ በአማራ ክልል ጦርነትና ወረራ መክፈቱን ተከትሎ ወደ ኮምቦልቻና ላሊበላ የሚደረገው በረራ ተቋርጦ የቆየ ሲሆን ሰኞ ታኅሣሥ 25 ወደ ላሊበላ የነበረው በረራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com