ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዳግም ወደ ላልይበላ በረራ ጀመረ

Views: 36

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላልይበላ የሚያደርገውን የሀገር ውስጥ በረራ በድጋሚ በዛሬው ዕለት ጀምሯል፡፡

አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት በላልይበላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት መፈጸሙን ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ አቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድጋሚ ወደ ላልይበላ የሚያደርገው በረራ በይፋ መጀመሩን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከአየር መንገዱ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com