ዜና

ሩሲያ 12 ስኬታማ የኃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች ሙከራ አደረገች

Views: 49
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን የዚርኮን ኃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች በተከታታይ ለ12 ጊዜ በማስወንጨፍ ሀገራቸው ስኬታማ ሙከራ ማድረጓን ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከሀገሪቷ እንዲሁም ከሣይንሥ እና ትምህርት ምክር ቤቶች ጋር በጥምረት ባደረጉት ስብሰባ ላይ እንደገለጹት ÷ ሚሳኤሉ እጅግ ዘመናዊ እና ማንኛውንም የምድርም ሆነ የአየር ላይ ዒላማ መምታት የሚችል ነው፡፡
ፕሬዚዳንቱ ሙከራው እጅግ ስኬታማ እንደነበረ ገልጸው፥ ለሀገራቸውም ትልቅ ኩነት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የሚሳኤሉን ንድፍ ለሠሩት፣ ላበለጸጉት እና በአጠቃላይ የኃይፐር ሶኒክ ሚሳኤሉን ስርዓት እውን ላደረጉት ኢንጂነሮች ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
የሚሳኤሉ መበልጸግ የሀገሪቷን የደኅንነት እና የመከላከያ ብቃት ለማሳደግ ዓላማ ያደረገ መሆኑን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com