ዜና

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

Views: 58
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ው ፔንግ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ማለትም ከግጭት በኋላ ስለሚደረገው መልሶ ግንባታ እና ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡
ሁለቱም ወገኖች ሀገራቱ በቀጣይ ሊሰሩባቸው የሚችሉ የትብብር ዘርፎችን መለዋወጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com