ዜና

በአፍሪካ እስካሁን ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል

Views: 64
ከ55 የአፍሪካ ሀገራት በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ9 ሚሊየን 505 ሺህ በላይ ሰዎች ሲደርሱ፥ በአህጉሪቱ ከ185 ሚሊየን 502 ሺህ በላይ ለሆኑ ሰዎች ክትባት መሰጠቱም ነው የተገለጸው፡፡
በአህጉሪቱ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ227 ሺህ በልጧል፡፡
በአንጻሩ ከ8 ሚሊየን 508 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ተነስቷል፡፡
ደቡብ አፍሪካ ከ3 ሚሊየን 417 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና በመያዝ በቀዳሚነት ስትነሳ ፥ በአገሪቱ ከ90 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ግብጽ እና ኬኒያ ከአህጉሪቱ ቫይረሱ የጸናባቸው አገራት እንደሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com