ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጅ ባለሀብቶች ድጋፍ አደረጉ

Views: 45
ሐምሌ 23 ቀነ3 2013 በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጅ ባለሀብቶች በአሸባሪው ጁንታ ላይ አይበገሬ ክንዳቸውን በማሳረፍ ላይ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ አባላት ድጋፍ አደረጉ፡፡
በራያ ግንባር ተሰማርተው ሽብርተኛውን የህወሐት ቡድን እየደቆሱ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት ለእርድ የሚሆኑ 1 ሚሊየን 575 ሺህ ብር ግምት ያላቸውን በቁጥር 63 ሰንጋ በሬዎቹን ነው ድጋፍ ያደረጉት።
አቶ ሰለሞን ሞገስ የበጎ ድጋፍ ተወካይ አስተባባሪ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት ፣ ለዓለም አቀፍ ህጎች ደንታ የሌለውን፣አሸባሪና ፀረ ህዝብ የሆነውን ይህን የጥፋት ቡድንን እያደባዩ ለሚገኙ የሀገርና የሕዝቦች መከታ፣ ዋልታና ማገር ለሆነው ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ይህይ ድጋፍ ስናደርግ ያኮራናል ብለዋል ፡፡
በአጠቃላይ ለሰራዊቱ ሊሰጡ ከተዘጋጁት 5 መቶ የእርድ ሰንጋዎች ውስጥ በመጀመሪያው ዙር 63ቱን አስረክበናል ብለዋል።
የደቡብ ዕዝ አዛዥ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ሁምኔሳ መርጋ ፣ ሀገር ወዳድ ደጀን ህዝብ ያለው ሠራዊት ሁሌም አሸናፊ ነው ፡፡ እናንተ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ያደረጋችሁት ድጋፍ ለሠራዊታችን የድል ሚስጥር ከመሆኑም በላይ የሞራል ስንቁ በመሆን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜና በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፅም ያስችለዋል ብለዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com