ዜና

የሰላም ሚኒስትሯ ከተመድ የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

Views: 36
 ሃምሌ 23፣ 2013  የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ዶክተር ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር ተወያዩ፡፡
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በውይይቱ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች በተለይም በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ከአንድ ወገን የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ ስላለው የሰብዓዊ እርዳታ አስመልክቶ በስፋት መክረዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ስለምትገኝበት የለውጥ ሂደት፣ በቅርቡ ስለተካሄደው የምርጫ ሂደት እና በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ላለፈው አንድ አመት በመካሄድ ላይ ስላለው ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ የምክክር ሂደትን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com