ዜና

በሄንኬን ኢትዮጵያ ስር የሚገኘው የሀረር ቢራ ፋብሪካ ለሀረር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ግማሽ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የስፖርት ትጥቅ ዛሬ አበርክቷል

Views: 34
በሄንኬን ኢትዮጵያ ስር የሚገኘው የሀረር ቢራ ፋብሪካ ለሀረሪ ክልል ስፖርት እድገትና ለማህበራዊ አገልግሎቶች መዳረስ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጠይቀዋል።
ፋብሪካው ለሀረር ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ያደረገውን ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚገመት የስፖርት ትጥቅ የርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ በቀለ ተመስገን ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ በመሳሰሉ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይም በስፋት እንዲሳተፍ ጥያቄ አቅርበዋል።
የክልሉ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አሚና አብዱከሪም በበኩላቸው ፋብሪካው ለክለቡ ያደረገው የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ለክለቡና ለክልሉ ስፖርት እድገት ትልቅ ትርጉምና አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ክለቡ በክልሉና ሀረር ቢራ ፋብሪካን በመሳሰሉ አጋር አካላት በሚደረግለት ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደከዚህ ቀደሙ በውጤት ሊታገዝ እንደሚገባው ያሰመሩበት ወ/ሮ አሚና የክለቡ ተጫዋቾች ግባቸው በፕሪምየር ሊግ መሳተፍ ሳይሆን በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና መሳተፍና ውጤታማ መሆን ሊሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
የሄንኬን ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሚስተር ሁበርት ኢዜ እና የሀረር ቢራ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ አቶ ምስጋናው ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ለሀረር ከነማ ቡድን ወደ ሦስት መቶ ሺህ ብር የሚገመት የስፖርት ትጥቅ ማበርከታቸውን አስታውሰው ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው በገቡት ቃል መሰረት በዛሬው እለት 500 ሺህ ብር የሚያወጡ ልዩ ልዩ የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶች መለገሳቸውን ገልጸዋል።
ፋብሪካው ልዩ ትኩረትና ቅድሚያ ሰጥቶ በ80 ሚሊዮን ብር ያስገነባው የፍሳሽ ማጣሪያ አለም የደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃና መስፈርት ያሟላ መሆኑን የተናገሩት የፋብሪካው ቴክኒካል ኃላፊ አበበ አለማየሁ በበኩላቸው ጉብኝቱ ግቡን የመታና ፋብሪካው ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ክፍተት መኖሩን ያረጋገጡበት እንደነበረ ገልጸዋል።May be an image of outdoors
ከዚህ በመነሳትም  ከሚመለከታቸው የክልሉ ተቋማት የመስተዳድር አካላትና ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በመቀራረብ ግንዛቤ የመፍጠርና ማህበራዊ ድጋፎችን የማጠናከር ተግባራት በስፋት እንደሚከናወኑ አረጋግጠዋል።በቀጣይነትም ከማዘጋጃ ቤቱ፣ ከክልሉ መንግስትና ከህብረተሰቡ ጋር ይበልጥ በመቀራረብ በስፖርት፣ በልማትና በማህበራዊ አገልግሎት አቅርቦቶች ሰፊ ድጋፍና ተሳትፎ እንደሚያደርጉም የሥራ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com