ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ሳምናታዊ መግለጫ ሰጥተዋል

Views: 46
ሐምሌ 22 ቀን 2013 ባለፉት ሳምንታት በችግር ውስጥ ከነበሩ ዜጎቻችን መካከል በሳኡዲ አረቢያ የነበሩ 41 ሺህ 873 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ሳምናታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው የፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ የተመለከቱ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡
በዚህም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምክትል ዋና ፀሐፊነት የፖለቲካና የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ሮዝመር ዲካርሎ ጋር በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብ እና በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አንስተዋል።
የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በተመለከተ፡ ኢንቨስትመንት በዋሽንግተን ዲሲ NNPA Newswire ለተሰኘ ጋዜጣ ፣ በኩዌት አል-ራይ ጋዜጣ ፣በፓሪስ በቴሌኮም ዘርፍ የኢንቨስትመንት የማስተዋወቅ ሥራ መከናወኑንና ከአውስትራሊያ ፎረስት ኪውር ሜታልስ ግሩፕ የተባለ ኩባንያ በኢነርጂ ዘርፍ ለመሰማራት እና ከኩዌት አል በደር ከተባለ አለም አቀፍ ኩባንያ ጋር በግብርና ፣በኢነርጂ፣በማዕድን ፣በቴሌኮም፣ በነዳጅ፣በቱሪዝምና በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት አሳይተው የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ተደርጓል ነው ያሉት።
በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ውይይት መካሄዱንና ክልላዊ እና አህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደት ለማምጣት የተመሰረተ እና ከነጻ ንግድ ቀጠና ወደ ፖለቲካ ውህደት ለማሸጋገር ግብ መጣሉ፤ የአፍሪካ የንግድ ድርሻ ከሌሎች አህጉራት አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ መሆኑን፣ የሚፈጥራቸው እድሎች፣ የሚያስገኛቸው ጥቅሞችና ሊያስከትል የሚችልባቸውን አሉታዊ ተጽእኖዎች ላይ ማብራሪያ መሰጠቱን ነው የገለጹት።
ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በተመለከተ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ከነበሩ ዜጎቻችን መካከል መንግስት የተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶችን በማዋቀር ባደረገው ጥረት 41 ሺህ 873 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡
በአሜሪካን ሃገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተቋቋመው ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር አስተባባሪነት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሃብት ለማሰባሰብና ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማሳየት ታላቅ የኢትዮጵያዊነት ትዕይንት በዋሽንግተን ዲሲ መካሄዱንና በወቅቱም ከ100ሺ ዶላር በላይ ማሰባሰብ መቻሉን አንስተዋል።
በጃፓን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ውድድርን እና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጃፓን ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይት መደረጉን፣ በኬንያ የሚገኙ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በአገራቸው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማሩ እና በአገራ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com