ዜና

ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት ስምምነት ተፈራረሙ

Views: 33
ሃምሌ 22 ቀን 2013  በኢትዮጵያና በሲዊዘርላንድ መካከል ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት የሚያስችል ስምምነት ዛሬ መፈራረማቸው ተገለፀ፡፡
የስምምነቱ አላማ የሲዊዘርላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ሀብታቸውን በልማት ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታትና የኢትዮጵያም ባለሀብቶች በሲዊዘርላድ ገበያ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ አስታውቀዋል፡፡
ተደራራቢ ግብር ለውጭ ኢንቨስትመንት ማነቆ በመሆኑ ከሲዊዘርላንድ መንግስት ጋር ሶስት ዙር ድርድር በማድረግ የተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የተደራራቢ ግብር ማስወገድ ስምምነት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማበረታት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ የግብር ማጭበርበርን በመከላከል ገቢ ለሀገር ልማትና እድገት እንዲውል የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለውም ይታወቃል፡፡
የተደራራቢ ግብር ማስወገድ ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የፈረሙት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሲሆኑ በሲዊዘርላንድ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የሲዊዘርላንድ አምባሳደር ታማራ ሞና ናቸው፡፡
የፊርማው ስነስርዓት ሲጠናቀቅም የሁለቱ ሀገራት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com