ዜና

በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ግድያን የሚቃወም ሰልፍ አካሄዱ

Views: 38
በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ግድያን የሚቃወም ሰልፍ አካሄዱ
ሰልፉን በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የስደተኞች ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ፊትለፊት ነው፡፡
ሰልፈኞቹ እንዳሉት በትግራይ ክልል ያሉ ኤርትራውያን እየተገደሉ ነው ሰብዓዊ መብታቸው እየተከበረ አይደለም ሲሉ ጠይቀዋል።
በትግራይ ክልል ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞች ከማንኛውም ጥቃት እንዲጠበቁ እና ስደተኞቹ የተሻለ የደህንነት ጥበቃ ወዳለበት እንዲወሰዱም ጠይቀዋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ክልል በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ስለመሆኑ አሳማኝ መረጃ አልኝ ብሏል።
በተለይም በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ስለመሆናቸውንም መግለጫው ጠቅሷል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com