ዜና

የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለቀጠናው እድገትና ትብብር መለያ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

Views: 61
 ሐምሌ 15 ፣ 2013  የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በአካባቢው ችግር ካለመፍጠሩ ባሻገር ለቀጠናው እድገትና ትብብር መለያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው በአረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መከናወኑን ገልፀዋል፡፡
ይህም በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ ችግር እንደማይፈጥር ጠቁመው ስጋት እንዳይኖርም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የህዳሴው ግድብ እውነተኛ ሀብት ሆኖ የጋራ ዕድገትና ትብብር መለያ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል ፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com