ዜና

ተሳፋሪዎችን ጭኖ ወደ ሶማሊያ ያቀና አንድ የኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን አደጋ ደረሰበት

Views: 60
ተሳፋሪዎችን ጭኖ ወደ ሶማሊያ ያቀና አንድ የኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ጌዶ በተባለው የሶማሊያ ክልል ኤል ዋክ አየር ማረፊያ ውስጥ አደጋ ደረሰበት፡፡
በስፍራው የነበሩ የነበሩ የዐይን እማኞችን ዋቢ አድርገው የሶማሊያ የዜና አውታሮች እንደዘገቡት ከሆነ አደጋው አውሮፕላኑ የአየር ማረፊያውን የማኮብኮቢያ መስመር ስቶ በመውጣቱ ነው ያጋጠመ ነው፡፡
አውሮፕላኑ 45 መንገደኞችን ጭኖ ነበር ተብሏል፡፡
የአውሮፕላኑ ንብረትነት መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው ‘ስካይ ዋርድ ኤክስፕረስ’ የተባለ የግል አየር መንገድ ነው ያለው የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በአደጋው የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አስታውቋል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com