ዜና

በቻይና ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ 12 ሰዎች ሞተው በርካቶች ተፈናቀሉ

Views: 66
ሃምሌ 14 ቀን 203 በማዕከላዊ ቻይና በጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ 12 ሰዎች ሲሞቱ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ፡፡
የማዕከላዊ ቻይና ዋና ከተማዋን ዣንግዡን ጨምሮ በሄናን ግዛት ውስጥ ከአስር በላይ ከተሞች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተጠቅሷል፡፡
በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚዘዋወሩ ምስሎች እንደሚያሳዩት ሰዎች ከደረታቸው ከፍ ባለ የውሃ መጠን በጎዳናዎች እና በባቡር ጣቢያዎች ላይ ሲጓዙ ያሳያል፡፡
የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ እንዳሉት በቻይና የጎርፍ መከላከል ሁኔታ በጣም አዳጋችና አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ፕሬዝደንቱ የጎርፍ አደጋው በሰው ህይወትና ንብረት ከፍተኛ ውድመት ማስከተሉን ገልጸው፤ ለሰው ህይወትና ንብረት ደህንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ መመሪያ መስጠታቸውን የአገር ውስጥ ሚድያዎች ዘግበዋል፡፡
94 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የሚኖሩበት የሄናን ግዛት ከፍተኛውን የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱም ተገልጿል፡፡
የአከባቢው ባለሥልጣናት የጎርፉ አደጋውን “በ100 ዓመት አንዴ” የሚፈጠር ክስተት ማለታቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com