ዜና

የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ድጋፍና አሸባሪውን ህወሓት የሚያወግዝ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው

Views: 45
ሐምሌ 14/2013  ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስከ ፍጻሜው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚደግፍና አሸባሪውን ህወሓት የሚያወግዝ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ከሲዳማ ክልል የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት በዚሁ ሰልፍ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
እንዲሁም የግህድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ የሚገልጹ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።
በአሸባሪው ህወሓት እና ተባባሪዎቹ የተቃጣብንን ጥቃት ለመመከትና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደጀን ለመሆን መዘጋጀታቸውን፣ በሚያስፈልገው ሁሉ ከመንግሥትና መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም የኢትዮጵያ አሸናፍነት እንዲረጋገጥ ቆርጠን ተነስተናል በማለት ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው።
የኢትዮጵያውያን ሠላምና አንድነት የሚፈታተነውን ጁንታ ለመጨረሻ ጊዜ ለማንበርከክ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መቆማቸውንም እንዲሁ።
ሰልፈኞቹ “ፈተናዎችን እየመከትን የተስፋ ብርሀናችንን ለማድመቅ እንሠራለን፣ የአሸባሪውን የህወሓት ትንኮሳ እናከሽፋለን፣ኢትዮጵያ ከፈተናዎቿ በላይ ኃያል ሃገር ናት” የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።
“ምዕራባዊያን እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ ያንሱ፣ የትግራይ ህዝብ አጋራችን ነው ፤ጁንታው ጠላታችን ነው” የሚሉ መፈክሮች ከፍ ብለው ተደምጠዋል።
”እኛን ሊለያይ፣ ሊበትን የሚችል ኃይል የለም፣ አይኖርምም ”ሲሉም ሰልፈኞቹ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎችም አመራሮች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልገሎት ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com