ዜና

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ‘የትግራይ ተወላጆች እየታሰሩ ነው’ በሚል ለፈጠረው የሃሰት ክስ የተጠቀመው ፎቶ የምርጫ ዕለት ከመራጮች ሰልፍ ላይ የተወሰደ መሆኑ ተጋለጠ

Views: 62
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ‘የትግራይ ተወላጆች እየታሰሩ ነው’ በሚል ለፈጠረው የሃሰት ክስ የተጠቀመው ፎቶ የምርጫ ዕለት ከመራጮች ሰልፍ ላይ የተወሰደ መሆኑ ተጋለጠ
ሐምሌ 10 ቀን 2013 አምነስቲ ኢንተርናሽናል ‘የትግራይ ተወላጆች እየታሰሩ ነው’ በሚል ለፈጠረው የሃሰት ክስ የተጠቀመው ፎቶ የምርጫ ዕለት ከመራጮች ሰልፍ ላይ የተወሰደ መሆኑ ተጋለጠ።
ፎቶ ግራፉን ያነሳው ግለሰብ አማኑኤል ስለሺ በትዊተር ገጹ ይፋ እንዳደረገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግስትን ለመወንጀል የተጠቀመው ፎቶ ግራፍ ከአውዱ ውጪ ትርጉም እንዲይዝ ተደርጎ ጥቅም ላይ መዋሉን አጋልጧል።
የምርጫውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ያለውን ሁኔታ ለማሳየት ተነስቶ ለኤኤፍፒ የተነሳው ፎቶ የትግራይ ተወላጆች እየታሰሩ ነው ለሚል ውንጀላ መዋሉ ስህተት መሆኑን በማመልከት ፎቶውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከገጹ ላይ እንዲያወርደው ጠይቋል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ላቀረበው ውንጀላም ተዛማጅ ፎቶ እንዲጠቀም አማኑኤል ስለሺ አመላክቷል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com