ዜና

በኢትዮጵያ በተካሄደው የኦንላይን ግብይት አንድ ኪሎ ግራም ቡና ከ14 ሺ ብር በላይ ተሸጠ

Views: 44
ሃምሌ 8፤2013 በባለ ልዩ ጣአም የቡና ውድድር አንድ ኪሎ ግራም ቡና ከ14 ሺ ብር በላይ ተሸጠ።
በቅርቡ በኢትዮጵያ በተካሄደው ባለ ልዩ ጣዕም ቡና የኦንላይን ግብይት አንድ ኪሎ ግራም ቡና 330 ዶላር (14ሺ 533) መሸጡን በዩኤስ. ኤይድ የኢትዮጵያ የካፍ ኦፍ ኤክሰለንሲ አስተባባሪ አስታወቁ፡፡
ከነዚህ አርሶ አደሮች መካከል ሰላሳ ዘጠኙ የተሻለ ቡና በማቅረብ በውድድሩ የመጨረሻ ዙር ተሳታፊ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በውድድሩ የመጨረሻ ዙር መቅረብ ያልቻሉት ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች ውድድሩ ቡናቸውን በጥራት እንዲያዘጋጁ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ጠቁመዋል፡፡
ባለስልጣኑ በውድድሩ የሚሳተፉ ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች ከምርታቸው ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት ድጋፍ ማድረጉንም አብራርተዋል፡፡
የካፕ ኦፍ ኤክሰለንሲ ውድድር በብራዚል እና በተለያዩ አገራት የሚካሄድ መሆኑን ያወሱት ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያ ባካሄደችው ሁለት ዙር ውድድር አንድ ኪሎ ግራም ቡና በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ የዓለምን ሪከርድ መያዟን አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በብራዚል በተካሄደ ውድድር አንድ ኪሎ ግራም ቡና 107 ዶላር የተሸጠ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ግን 300 ዶላር መሸጡ ከፍተኛ ስኬት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዘንድሮ ውድድር ላይ አሸናፊ የሆኑትን ቡናዎች ለመግዛት በ26 አገሮች የሚገኙ 140 የቡና ንግድ ኩባንያዎች በጨረታው ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com