ዜና

ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሽልማት ተበረከተላቸው

Views: 45
ሐምሌ 08/2013 ዓ.ም  በህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ጉዳይ የአደራዳሪነት ሚናው ወደ አፍሪካ ሕብረት እንዲመለስ የማሳመን ሥራ ለሠሩት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ሽልማት ተበረከተላቸው።
በጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት የአደራዳሪነት ሚናው ወደ አፍሪካ ሕብረት እንዲመለስ ለተጫወቱት ሚና ለዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የምስጋና መርኃግብር እየተካሄደ እንደሚገኝ ኢብኮ ዘግቧል።
ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በማብራሪያቸው ግድቡ በኢትዮጵያ ከ65 ሚሊየን በላይ ዜጎች መብራት እንዲያገኙ እና ከድህነት እንዲወጡ የማድረግ ዓላማን ብቻ ያነገበ መሆኑን አስረድተዋል።
ግድቡ ለኢትዮጵያውያን የሕልውና ጉዳይ መሆኑን በማስረገጥ ትልቅ የዲፕሎማሲ ሥራ በማከናወናቸው ሚኒስትሩ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፈዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com