ዜና

የጥፋት ሃይሎችን “በቃችሁ” በማለት ለኢትዮጵያ ልማት፣ ሰላምና መረጋጋት ወጣቶች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

Views: 47
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6/2013 ወጣቶች የጥፋት ሃይሎችን እኩይ ዓላማ በማክሸፍና “በቃችሁ” በማለት ለኢትዮጵያ ልማት፣ ሰላምና መረጋጋት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ የምዕራብ እዝ ምክትል አዛዥና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አባል ብርጋዴር ጄኔራል አለማየው ወልዴ አሳሰቡ።
ከኮማንድ ፖስቱ፣ ከመተከል ዞንና ከቡለን ወረዳ የተውጣጡ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶች በወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ውይይት አካሂደዋል።
የምዕራብ እዝ ምክትል አዛዥና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አባል ብርጋዴር ጄኔራል አለማየው ወልዴ፤ ”ያለፈውን ጥፋት እያነሱ ነገሮችን ከማባባስ ይልቅ ሰላም የሚመጣው በሰላማዊ መንገድ ብቻ መሆኑን በመረዳት ለቀጣይ አብሮነትና አስተማማኝ ሰላም መስራት ይገባል” ብለዋል።
በመተከል ዞን ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሁለት ዙር የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሩ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com