ዜና

የናይጄሪያና የጂቡቲ ፕሬዚዳንቶች በኢትዮጵያ በምርጫው ለተገኘው ድል የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ

Views: 41
ሐምሌ 06 ቀን 2013  የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ እና የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በኢትዮጵያ በምርጫው ለተገኘው ድል የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትም በተመሳሳይ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንት ቡሃሪ በዶክተር አቢይ አህመድ የሚመራው ፓርቲ በምርጫው አብላጫ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር በማግኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን በናይጄሪያ ህዝብ ስም ገልጸዋል።
በመልዕክታቸውም “በምትከተሉት ጥሩ ፖሊሲ አማካኝነት የህዝባችሁን ኑሮ ለመለወጥ መስራታችሁን መቀጠል አለባችሁ” ብለዋል።
የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ጊሌ በበኩላቸው የምርጫው በሰላም መጠናቀቅ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የሁለቱ አገሮች እህትማማችነት ይበልጽ እንደሚጠናከርም ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በበኩላቸው ለዶክተር አቢይ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ የብልጽግና ፓርቲ በክልልና በፌዴራል ደረጃ በማሸነፉ ‘እንኳን ደስ አላችሁ’ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለምርጫው ስኬታማነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ችረዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com