ዜና

ፕሬዚዳንት ራማፎሳ አሜሪካ ባዘጋጀችው የዴሞክራሲ ስብሰባ ላይ እንደማይካፈሉ ተገለፀ

Views: 68
አሜሪካ ባዘጋጀችው የዴሞክራሲ ስብሰባ ላይ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እንደማይካፈሉ የፕሬዚዳንት ጽኅፈት ቤቱ ሚኒስትር ሞንድሊ ጉንጉቤሌ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ አሜሪካ በምታዘጋጀው እና በምትመራው ስብሰባ ላይ የማይሳተፉበት ምክንያት እንዳልታወቀም ነው የተመላከተው፡፡
አሜሪካ ባዘጋጀችው የዴሞክራሲ ስብሰባ ላይ ከቻይና እና ሩሲያ በተጨማሪ ዚምባቡዌ እና ኢትዮጵያም እንዳልተጋበዙና እንደማይሳተፉ ነው የታወቀው፡፡
ከስብሰባው አዘጋጆች እንደተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በዴሞክራሲ ላይ የሚካሄዱትን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ስብሰባዎች ይመራሉ ነው የተባለው፡፡
ከዚህ ቀደም ፓኪስታን በስብሰባው ላይ እንድትካፈል ብትጋበዝም እንደማትሳተፍ መግለጿ ይታወሳል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com