ዜና

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር ተወያዩ

Views: 177

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከካርቱም አልኒሊን እና ከሱዳን ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር ተወያዩ።
ውይይቱም በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካካል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ተግባራት ዙሪያ መሆኑ ተመላክቷል።
ውይይቱ ከዚህ ቀደም ከዶክተር ኦመር አለሚን ጋር ከነበረው የሁለቱ አገራት ምሁራን በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍንና በሕዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት ይጠናከር ዘንድ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችሉ ተጨባጭ ሃሳቦችን ከማፍለቅና በመተግበር ረገድ ሊከናውኑ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከተደረገው ምክክር የቀጠለ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com