ዜና

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉዳይ ላይ ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

Views: 55

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ጋር በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉዳይ ላይ ተወያዩ።

የእንግሊዝ አምባሳደር እና ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ያደረጉት ውይይት በአፍሪካ ቀንድ እና በቀጠናው የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ከውይይቱ በኋላ እንደተናገሩት፣ አገራቸው እኤአ 2020 ጀምሮ ከአፍሪካ አገራት ጋር እንደ አዲስ በመቃኘት የጀመራቸውን የግንኙነት ምዕራፍ በመርህ ላይ ተመስርቶ ለማስኬድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ጉልህ ሚና ይጫወታል።

እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ስትራቴጂክ አጋርነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገርም በወታደራዊና የሰላም እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በቅርቡ በትግራይ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ በአገሪቱ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሂደትና ለቀጣናው ዙሪያ-መለስ ሰላምና ደህንነት አስተዋፅዎ ያበረከተ መሆኑን የተናገሩት አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል፣ በቀጣይ ከሚካሄዱ አገራዊ ሁነቶችና ሌሎች ጉዳዮች አንፃር የእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄ/ል ብርሀኑ ጁላ በበኩላቸው፣ አገሪቱ ካለችበት አሁናዊ ሁናቴ አንጻር ከቀጠናው አገራት ጋር ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነት በማጤን ለዘላቂ ሰላም በትኩረት በመሰራት ላይ መሆኑን ገልፀው፣ በአህጉራዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

ሰራዊቱም የአገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በአስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠውላቸዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com