ዜና

በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን በተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

Views: 80

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ታጣቂዎች በተሽከርካሪዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ ጥቃቱ ትናንት ከምሽቱ 4:30 አካባቢ ነው በኩዩ እና በደገም ወረዳዎች መካከል ለጊዜው ባልታወቁ ታጣቂዎች የተፈጸመው፡፡

ጥቃቱ ትናንት ምሽት ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ሲጓዙ በነበሩ የአይሱዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው የተፈጸመው፡፡

ጥቃቱ ምሽት 4፡30 አካባቢ ለጊዜው ባልተያዙ እና ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው ሲሉ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ለኢቢሲ ማብራሪያ የሰጡት የዞኑ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ቅናጢ ጫላ፣ በደገም እና ኩዩ ወረዳዎች መካከል በ6 የአይሱዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ተመሳሳይ ወንጀል መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com