ዜና

የቆቦ ከተማ ለግል ታጣቂዎች ሥልጠና ሰጠ

Views: 65

የቆቦ ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ጽህፈት ቤት የግል ታጣቂዎችን ሥልጠና ሰጠ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ደሳለ ዋክሹም እንደገለጹት የስልጠናው ዓላማም የግል ታጣቂዎችን በሻለቃ፣ በመቶ፣ በሻምበል እና በጋንታ በማደራጀት የአካባቢውን ጸጥታ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር (ማለትም ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ከፖሊስ እና ሚኒሻ ጋር) በመሆን የበርና የከተማ የዉስጥ ለውስጥ ጥበቃ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስጠበቅ ታስቦ የተሰጠ መሆኑን ጠቁመው፣ ሥልጠናውም በተከታታይ እንደሚሰጥም ገልፀዋል፡፡

ስልጠናውን ሲወስዱ ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች ስምምነት በማድረግ ያለምንም ወጭ ወደ ስልጠናው የገቡ መሆኑን ተናግረው በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ተጠቅመው ማህበረሰቡን ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሁሉም የጸጥታ አካላትም ስልጠና በመውሰድ የተሻለ አደረጃጀት እንዲፈጠር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com