ዜና

ሰሜን ምስራቃዊ ህንድ በከባድ ርዕደ መሬት ተመታ

Views: 43

አሳም ተብሎ የሚጠራው የሰሜን ምስራቃዊ ህንድ አካባቢ ከባድ ርዕደ መሬት ተመታ፡፡ በሬክተር ስኬል 6.0 ማግኔትዩድ ተለክቷል የተባለለት ርዕደ መሬቱ ህንድ ከቡታን በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ ያጋጠመ ነው፡፡

በ150 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው ጉዋሃቲ የተሰኘች የአሳም ግዛት ዋና ከተማ ላይ ጉዳት አድርሷል የተባለ ሲሆን፣ ግንባታዎች እና መሰረተ ልማቶች መጎዳታቸው ተነግሯል፡፡

ሆኖም፣ ሰብዓዊ ጉዳቶች ስለመኖራቸው የተገለጸ ነገር የለም፡፡ ህንድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እጅጉን በመፈተን ላይ ትገኛለች፡፡ እስካሁንም ከ200 ሺ የሚልቁ ሰዎች ህይወት አልፏል መባሉ የሚታወስ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com