ዜና

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ወራት በኋላ የኢንተርኔት አገልግሎት አገኘ

Views: 40

በትግራይ ክልል በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ኢንተርኔት ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ካምፓሶች ከትላንት ምሽት ጀምሮ ኢንትርኔት አገልግሎት መለቀቁን የዩኒቨርሲቲው መምህራን ተናግረዋል፡፡

በትግራይ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠው ክልሉን በሚመራው ህወሓትና በፌደራል መንግስት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ውጊያ ማምራቱን ተከትሎ ነበር፡፡

የፌደራል መንግስት ህወሓት በክልሉ የሚገኘውን የሰሜን እዝ በማጥቃት ክህደት ፈጽሟል በማለት በክልሉ “የህግ ማስከበር ዘመቻ” ከጀመረ በኋላ፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ ነበር፡፡

የኢንተርኔት መቋረጥ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ መፍጠሩን መምህራኑ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

የኢንትርኔት አገልግሎት አለመኖሩ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማለትም በአሪድ፣ዓይደር፣ መለስ እና ዓዲ ሓቂ ካምፓሶች የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ተፅእኖ ፈጥረዋልም ነው ያሉት መምህራኖቹ፡፡

መምህራኑ “ኢንተርኔት ባለመኖሩ ምክንያት በተለይም የድህረ-ምርቃ ትምህርት ለመስጠት ተቸግረናል” ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com