ዜና

የሰራዊቱን መለዮ ለብሰው በአምልኮ ስፍራዎች በሚገኙ የመከላከያ አባላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ

Views: 43

የሰራዊቱን መለዮ ለብሰው በሐይማኖት እና ማምለኪያ ስፍራዎች በሚገኙ አባላቱ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡ መከላከያ አባሎቹ መለዮ ለብሰው በሐይማኖት ማምለኪያ ስፍራዎች እንዳይገኙም ከልክሏል፡፡

የእምነት ተቋማቱ ለምን መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ክትትል እንደሚያደርግም ነው ያስታወቀው።

የአገር መከላከያ ሰራዊት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው “ሠራዊቱ ገለልተኛ፣ ዩኒፎርምም ሆነ ሀይማኖት የሌለው” መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊት ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የማይወግን እና የማንኛውንም ዕምነት የማያራምድ መሆኑ በህገ- መንግስቱም ይሁን በቅርቡ በጸደቀው የመከላከያ ስትራቴጂክ የግንባታ ሰነድና በአስተዳደራዊ ደንቡ ላይ በግልጽ ተደንግጓልም ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ይሁን እንጂ በቅርቡ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም በመልበስ በተለያዩ የዕምነት ተቋማት ሲያመልኩ የሚያሳይ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡ ይህ ድርጊት በሚመለከታቸው የተቋሙ የፍትህ አካላት ተጣርቶ ርምጃ እንደሚወሰድ አረጋግጠዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com