ዜና

በናይጀሪያ ለ12 ተከታታይ ቀናት በኮሮና የሞተ ሰው የለም ተባለ

Views: 41

በናይጀሪያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ለተከታታይ 12 ቀናት በቫይረሱ ምክንያት የሞተ ሰው አለመኖሩ ተዘግቧል፡፡

በቫይረሱ አዲስ 51 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ በአጠቃላይ የተጠቂዎችን ቁጥር 164 ሺ ከፍ አድርጎታል፤ ከኮሮና ጋር በተያያዘ 2061 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ሀገሪቱ ከፈረንጆቹ የካቲት 27 ጀምሮ 1.87 ሚሊዮን ምርመራ ያደረገች ሲሆን፣ የዜጎቿም በማህበራዊ ተቋማት ጥንቃቄ እንዲደርጉ መክረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com