ዜና

የደቡብ ዕዝ የጊዜ ቆይታቸውን የሸፈኑ እና የተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም ለነበራቸው የዕዙ አባላት የማዕረግ ሹመት ሰጠ

Views: 42

ሚያዚያ 18 ቀን 2013 የአገር መከላከያ ሰራዊት ደቡብ ዕዝ ለድጋፍ ሰጪ የበታች ሹሞች፣ ለመስመራዊና ለከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ሰጥቷል።
በዚሁ የማዕረግ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የዕዙ ኮማንድ አካላትና በየደረጃቸው የሚገኙ መምሪያና ክፍል ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የዕዙ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ ባስተላለፉት መልዕክት “የነበሩብንን ጥቃቅን ድክመቶቻችንን አርመን ጥንካሬዎቻችንን አቅበን አንፀባራቂ ግዳጅ አፈፃፀም እንደነበረን ያየንበት፣ ውስጣዊ አንድነታችንን በፈተሽንበት መድረክ ማግስት ይህ የማዕረግ ሹመት መደረጉ ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል።

ዕዙ በተሠማራበት ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ግለቱን ጠብቆ እንዲሳለጥ በማድረግ ረገድ ድጋፍ ሰጪ ዩኒቱ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል።

የዕዙ ዋና አዛዥ በዚሁ ሥነ ስርዓት ላይ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ፣ የምስራቅ አፍሪካ ጂኦ ፖለቲካዊ አንድምታ፣ የህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ወቅት ዕዙ ስለነበረው ላቅ ያለ ግዳጅ አፈፃፀም አስረድተዋል።

የተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም ህዝብና መንግሥትን ለመነጣጠል ብሎም የሠራዊቱን ስም ለማጠልሸት ያገኙትን አማራጭ ሁሉ እየተጠቀሙ ቀን ከሌት እያሤሩ ያሉ ስለመሆናቸው ገልጸው፤ ሠራዊቱ ለዚህ ምቹ እንዳልሆነና ተልዕኮውን ብቻ የሚወጣ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com